SplitEase+

ወጪ ለማከል ደረሰኝ እንዴት መቃኘት እችላለሁ?

ደረሰኝ መቃኘት ጠቅላላውን መጠን እና ዝርዝሮቹን ከደረሰኙ ያነባል፤ እርስዎ መጻፍ አያስፈልግዎትም። የSplitEase+ አካል ነው።

ደረጃዎች

  1. + አዝራሩን ይንኩ፣ ከዚያ ቃኝ (Scan)ን ይንኩ።
  2. የደረሰኙን ሙሉ ፎቶ ያንሱ፣ ወይም ያለዎትን ፋይል ለመጠቀም የፎቶ ማዕከል (Library)ን ወይም PDFን ይምረጡ።
  3. SplitEase ያገኛቸውን ዝርዝሮች ያረጋግጡ እና ተጠቀም (Use)ን ይንኩ።
  4. ማን እንደከፈለ እና እንዴት እንደተከፋፈለ ይገምግሙ፣ ከዚያ አስቀምጥ (Save)ን ይንኩ።

ምስሉ እንዲነበብ ወደ SplitEase ይሰቀላል። እንዴት እንደሚያዝ ለማወቅ የግላዊነት ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።

ቅኝቶች ሊሳሳቱ ይችላሉ። ከማስቀመጥዎ በፊት ሁልጊዜ መጠኑን ያረጋግጡ።

የSplitEase መተግበሪያ በዚህ ቋንቋ ገና አይገኝም። በቅንፍ ውስጥ ያሉት የአዝራር ስሞች በማያ ገጹ ላይ የሚያዩዋቸው ናቸው።

ተዛማጅ ጥያቄዎች

አሁንም እገዛ ይፈልጋሉ?

ይጻፉልን፤ ከSplitEase ቡድን አንድ ሰው ምላሽ ይሰጥዎታል።

ድጋፍ ሰጪን ያግኙ
ቋንቋ: አማርኛ